Watch ዐረገ በስብሃት Erget Ethiopian Orthodox Tewahedo Mezmur about Ascension of Jesus Christ on WongelTube Ethiopian Orthodox Tewahido Website
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም ዕርገቱን ለመናገር ከሰማየ ሰማያት መውረዱን አስቀድሞ ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ማንም ወደ ሰማይ የወጣ የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው ብሎ ከዕርገቱ በኋላ በየማነ አብ፤ በዝባነ ኪሩብ በአምላክነት ሥልጣን ለመኖር ወደሰማይ የወጣ ከእርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ አስረግጦ ነገረን፡፡ ሲጀምር ከሰማይ መውረዱን ማስቀደሙ ወረደ ብሎ ዐረገ ለማለት ይመቻል፡፡ ተጸነሰ ተወለደ ለማለት ጥንቱ ከሰማያት ወረደ ማለት እንደሆነ ሁሉ፤ ‘ተሰቀለ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ ተነሣ’ ለማለት ‘ጥንቱ:- ተጸነሠ፤ ተወለደ፤ አደገ ተመላለሰ ሠላሳ ዓመት ኖረ የሚለው ነው፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ዮሐንስ ጠርዝና ጠርዙን ይዞ ተናገረ፡፡ ወረደ ዐረገ የሚሉት ሁለት ቃላት የዓለም ድኅነት መነሻና መድረሻ ናቸው እነዚህን ሁለት ቃላት ስናይ በሁለቱ መካከል የተፈጸሙትን የአምላክ ሥራዎች ልብ ማለት ይገባል፡፡ ቤት በመሠረት ይጀመራል በጣሪያ ይፈጸማል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ይህን የቤዛነት ሥራ ሲያስረዳ በዮሐ.1፥14 “ቃል ሥጋ ኮነ” ቃል ሥጋ ሆነ ብሎ ጀምሯል ይህንም ቃል ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም በማለት ሰው መሆኑን ብቻ ሳይሆን በአርያም የሚኖር መሆኑን አስተማረን፡፡ እንግዲህ ጌታችን ዕርገት እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አለመሆኑን ቀድሞ በነቢያት የተነገረ ኋላም በሐዋርያት የተመሰከረ መሆኑን ማወቅ ያስፈለጋል፡፡
Song ሰላምን እተውላችኋለሁ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ
እኔ የምሰጣችሁ አለም እንደሚሰጠው አይደለም
ልባቹ አይደንግጥ አትፍሩም ዮሐ 14:27
የቻነላችን አባል መሆንዎትን እንዳይዘነጉ [Please subscribe to our YouTube Channel here]: https://www.youtube.com/keraniyo
Ethiopian Orthodox Mezmur Tewahedo collection
Christian life and faith.
በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፥19). በማህበረ ቅዱሳን የተዘጋጀ
አዳዲስ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች እና ስብከቶችን ይመልከቱ:: ለጉዋደኞችዎም በማካፈል ሃይማኖትዎን ያስፋፉ: ያጠንክሩ: ወንጌልቲዩብ የተዋህዶ መዝሙር ድረ-ገጽ
Watch Latest Ethiopian Orthodox Mezmure and Sibket Videos – Share this video with your friends to spread the word of God and strength Ethiopian Orthodox Tewahido.
Like WongelTube on Facebook. Don’t Miss the new Mezmur.