Watch Tewodros Yosef(ሊቀመዘምራን)-Atlef│አትለፍ│New Ethiopian Orthodox Mezmur 2018 on WongelTube Ethiopian Orthodox Tewahido Website
✞✞✞• #አትለፍ °✞✞✞
አባቶችን ጠይቅ ይነግሩሃል
የእምነትን ምስጢር ያስረዱሃል
አትለፍ የተዋህዶን ድንበር
በውጪ ተጥለህ እንዳትቀር
✞✞✞•°°°•✞✞✞°•••°
የአብና የወልድ የመንፈስቅዱስን
ሦስትነቱን አምነን ፍጹም አንድነቱን
ቅዱሳት መጻህፍት እንደመሰከሩ
የሥላሴ አኗኗር ድንቅ ነው ምስጢሩ
አትለፍ የተዋህዶን ድንበር
በውጪ ተጥለህ እንዳትቀር
✞✞✞•°°°•°•••°✞✞✞
የአምላክን ሰው መሆን የስጋዌን ነገር
የዓለሙን ድኅነት ተዋህዶ ትመስክር
ያለመደባለቅ ያለመቀላቀል
ስጋን መዋሀዱን ከማርያም ድንግል
አትለፍ የተዋህዶን ድንበር
በውጪ ተጥለህ እንዳትቀር
✞✞✞•°°°•°•••°✞✞✞
የመቅደሷ ስርዓት በውስጧ የሚታየው
የተዋህዶ ነገር ምንጩ ከሰማይ ነው
ትርጉሙን ተረዱ ምስጢሩን ጠይቁ
በኑፋቄ ገመድ እንዳትታነቁ
አትለፍ የተዋህዶን ድንበር
በውጪ ተጥለህ እንዳትቀር
✞✞✞•°°°•°•••°✞✞✞
በፀበል በመስቀል በእምነት ሲታበሱ
በውስጧ ይገኛል የእግዚአብሔር ፈውሱ
ያለመጠራጠር በእምነት ቅረቡ
የመለኮት ስራ ብዙ ነው ጥበቡ
አትለፍ የተዋህዶን ድንበር
በውጪ ተጥለህ እንዳትቀር
✞✞✞•°°°•°•••°✞✞✞
ዓለሙን ሊያሳልፍ ይመጣል ዳግመኛ
በፍርዱ ወንበር ፊት እንቆማለን እኛ
በመለኮት ስልጣን በክብር ይገለጣል
አማላጅ አይደለም ኢየሱስ ይፈርዳል
አትለፍ የተዋህዶን ድንበር
በውጪ ተጥለህ እንዳትቀር
✞✞✞•°°°•°•••°✞✞✞
አዳዲስ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች እና ስብከቶችን ይመልከቱ:: ለጉዋደኞችዎም በማካፈል ሃይማኖትዎን ያስፋፉ: ያጠንክሩ: ወንጌልቲዩብ የተዋህዶ መዝሙር ድረ-ገጽ
Watch Latest Ethiopian Orthodox Mezmure and Sibket Videos – Share this video with your friends to spread the word of God and strength Ethiopian Orthodox Tewahido.
Like WongelTube on Facebook. Don’t Miss the new Mezmur.