Watch Ethiopian orthodox tewahdo mezmur ቅድስት አርሴማ on WongelTube Ethiopian Orthodox Tewahido Website
ቅድስት አርሴማ ሰማዕት ዘአርማንያ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ቅዳሳን አባቶቻችን ከፃፋት ከስንክሳር መፅሐፍ ይኸውም በታህሳስ ወር ስድስት ቀን የተገኘውን የብፅዕት የቡርክት ቅድስት አርሴማን የገድል ዜና እንናገራለን፡፡
በዚህች ዕለት የቅድስት ሰማዕት አርሴማ የቤተክርስቲያንዋ ቅዳሴ ከእርሷም ጋር የተገደሉ የሃያ ሰባት የቅዱሳን ሰማዕት የስጋ ፍልሰትና ሰማዕት የሆኑ የእነዚያ ደናግል መታሰቢያ ሆነ፡፡
ንጉስ ድርጣድስም ይህችን ቅድስት አርሴማን ከእኛ ጋር ስትኖር ይህንን ያህል እውቀት በልብሽ የለውምን አላት ፡፡ ቅድስት አርሴማም ድርጣድስን ሰነፍ የሰማይ ኑሮ ይበልጣል ይሻላልም አለችው፡፡ ያን ጊዜም ንጉስ ድርጣድስ ወደ መገደያው ቦታ እንዲወስዷአትና ራቁትዋን አድርገው በሰይፍ አንገትዋን እንዲቆርጧአት አዘዘ፡፡ እርሱዋም በመንግስት ሰማያት የክብር አክሊልን ተቀበለች፡፡
ከቅድስት አርሴማ ገድል ከምዕራፍ ሰባት ታምር የተወሰደ
በግፅብ ከተማ በእስክድርያ ስሙ እንስጣስዩስ የሚባል ቴዎዶስዩስ የሚሉት አንድ ንጉስ ነበረ፡፡ የጵጵስና ስሙ ይህንን አለም የናቀና የእግዚአብሔርን መንገድ የተከተለ ብፁአዊ ሙሴ ነው፡፡ ይችውም የምንኩስና ህግ ናት እርሱም የቅዱሳን ሰማዕታትን የፃድቃንን አጥንቶች ይሰበስብ የገድለቸውን ዜና ይጽፍ ቤታቸውንም ይሰራ ታቦታቸውን ያገባ በበአላቸው ይቀድስ ሁልጊዜም ታቦቶቻቸውን ይጉበኝ ነበር ፡፡
ከዕለታት በአንድ ቀንም ታቦትን ለማሰናዳትና ሜሮን ለመቀባት ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ ሲዳስስ በወርቅ የተለበጠና በላዮ በሮማይስጥና በፅርዕ ቋንቋ የብፅዕይት ቅድስት አርሴማ ስም የተፃፈበትን ፅላት አገኘ፡፡
ያን ጊዜም የቅዱሳንን ስማቸውን አሰበ፡፡ የገድላቸውንም ዜና መረመረ የብፅዕይት ንፅይት ቅድስት አርሴማን የሞትዋን ዜና አላገኘም፡፡ ስለዚህም ነገር በምን ዘመን ሰማዕት እንደሆነች የብፅዕት ቅድስት አርሴማን ስራ ያስረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ለመነ ማለደ ፡፡ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክት ተገለፀለት እንዲህም አለው ብፁአዊ ሙሴ ሆይ የብፅዕት ቅድስት አርሴማን ስራ እነግር ዘንድ ስማ ይቺ ሰማዕት ዛሬ አልተፀነሰችም ገና አልተወለደችም በወርቅ አምድ በህይወት መፅሐፍ ስሟ ተፅፏል እንጂ ነብዮ በመፅሐፍ ውስጥ ሁሉ ይፃፋል እንዳለው እርሷም በኃላኛው ዘመን ሰማዕት ትሆናለች በአለም ዳርቻ ሁለ የገድሏ ዜና ይታወቃል የሚበዛውም በነፃ አውጪ አገር ኢትዩጵያ ነው ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብፅይት ቅድስት አርሴማ የስም መታሰቢያ መጥራት አትተው፡፡ ፅላቷም ከአንተ ጋር ይኑር የመቅደሷ ህንፃ በህንፃ ቦታህ ጉን ይኑር ፡፡ ስምህም በተጠራበትም የሷ መታሰቢያ ይጠራል ይህንንም ብሎ ያ መልአክ ተሰወረ ወደ ላከውም ተመለሰ፡፡ እርሱም የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፡፡
ፀሎትና በረትዋ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን
አዳዲስ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች እና ስብከቶችን ይመልከቱ:: ለጉዋደኞችዎም በማካፈል ሃይማኖትዎን ያስፋፉ: ያጠንክሩ: ወንጌልቲዩብ የተዋህዶ መዝሙር ድረ-ገጽ
Watch Latest Ethiopian Orthodox Mezmure and Sibket Videos – Share this video with your friends to spread the word of God and strength Ethiopian Orthodox Tewahido.
Like WongelTube on Facebook. Don’t Miss the new Mezmur.